Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 22:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱም እግዚአብሔርን፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔርንም ‘አትድረስብን! ሁሉን ቻይ አምላክም ምን ያደርግልናል?’ አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነርሱም ሁሉን የሚችለውን አምላክ፦ ‘ከእኛ ራቅ፤ ምን ልታደርግልን ትችላለህ?’ አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ያደ​ር​ገ​ናል? ሁሉን የሚ​ችል አም​ላ​ክስ ምን ያመ​ጣ​ብ​ናል? ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔርንም፦ ከእኛ ዘንድ ራቅ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል? አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 22:17
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩንም አይጥለውም፥ ላማቸውም ትወልዳለች፥ አትጨነግፍም።


የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በጌታም ታመኑ።


በስምህ እንድናገር ወደ ፈርዖን ከሄድኩ ጀምሮ፥ ይህን ሕዝብ አስከፍቶታል፤ አንተም ሕዝብህን ከቶ አላዳንኸውም” አለ።


ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፥ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ” ይሏቸዋል።


እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙን መጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ ፊት ኀዘንተኞች ሆነን መሄድ ምን ይጠቅመናል?


እነሆ እንዲህ እያሉ ጮኹ “የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?”


እነሆ ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድ ለመኑት።


እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ እግዚአብሔር ተገቢ ያልሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች