ኢዮብ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ከሩቅም ሆነው ዓይናቸውን ባነሡ ጊዜ አላወቁትም፤ ድምፃቸውንም አሰምተው አለቀሱ፥ እያንዳንዳቸውም መጐናጸፊያቸውን ቀደዱ፥ ወደ ላይም ወደ ራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እነርሱም ከሩቅ ሆነው ሲመለከቱት እርሱ መሆኑን ሊለዩ አልቻሉም፤ በዚህ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ልብሳቸውንም ቀድደው በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ገና በሩቅ ሳሉ ኢዮብን አዩት፤ ሆኖም እርሱ መሆኑን በቀላሉ ለይተው ሊያውቁት አልቻሉም። በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ትቢያ ወደ ሰማይ እየበተኑና በራሳቸውም ላይ እየነሰነሱ በመጮኽ ማልቀስ ጀመሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ከሩቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላወቁትም፤ በታላቅ ድምፅም ጮኸው አለቀሱ፤ መጐናጸፊያቸውንም ቀደዱ፥ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ከሩቅም ሆነው ዓይናቸውን ባነሡ ጊዜ አላወቁትም፥ ድምፃቸውንም አሰምተው አለቀሱ፥ እያንዳንዳቸውም መጐናጸፊያቸውን ቀደዱ፥ ወደ ላይም ወደ ራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ። ምዕራፉን ተመልከት |