ኤርምያስ 35:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚህች ምድር በመጣ ጊዜ፦ ‘የከለዳውያንን ሠራዊትና የሶርያውያንን ሠራዊት በመፍራት ኑ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ’ አልን፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይህችን ምድር በወረረ ጊዜ፣ ‘ኑ፤ ከባቢሎን ሰራዊትና ከሶርያ ሰራዊት ሸሽተን ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ’ ተባባልን፤ ስለዚህም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ አገሪቱን በወረረ ጊዜ ከባቢሎናውያንና ከሶርያውያን ሠራዊት ሸሽተን እናመልጥ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣት ወስነናል፤ አሁንም በኢየሩሳሌም የምንኖረው ስለዚህ ነው።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በዚች ምድር ላይ በዘመተ ጊዜ፦ ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሶርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ፤ አልን፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚህች ምድር በመጣ ጊዜ፦ ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሶርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ አልን፥ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን። ምዕራፉን ተመልከት |