Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 65:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነሆ፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁ፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፥ ትውስታቸውም አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “እነሆ፤ እኔ፣ አዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፤ ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤ አይታወሱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እኔ አዳዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፤ ከዚህ በፊት የነበሩት ሁሉ ይረሳሉ፤ አይታሰቡምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “እነሆ፥ አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር ይሆ​ና​ልና፤ የቀ​ደ​ሙ​ትም አይ​ታ​ሰ​ቡም፤ ወደ ልብም አይ​ገ​ቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነሆ፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፥ የቀደሙትም አይታሰቡም፥ ወደ ልብም አይገቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 65:17
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የፊተኛውን ነገር አታስታውሱ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ።


እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


ሰማያትን እንድዘረጋ ምድርንም እንድመሠርት፥ ጽዮንንም፦ “አንቺ ሕዝቤ ነሽ” እንድል ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፥ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።


እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል ጌታ።


በምድርም ላይ በበዛችሁና በበረከታችሁ ጊዜ፥ ይላል ጌታ፥ በዚያ ዘመን፦ “የጌታ የቃል ኪዳኑ ታቦት” ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስታውሱትም፥ አይሹትምም፤ በድጋሚም አይሠራም።


ነገር ግን እንደተጻፈው፥ “ዐይን ያላየውን፤ ጆሮም ያልሰማው፤ በሰውም ልብ ያልታሰበው፤ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው፤”


ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል!


ዳሩ ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት ፍጡራን ነገሮች እንደሆኑና እንደሚለወጡ ያሳያል።


ነገር ግን እኛ ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች