Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 49:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ የተወለደው ሕጻን ልጇን ትረሳለች? ርህራሄ አልባስ እስክመሆን ትደርሳለች? አዎን፥ እርሷ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፦ “እናት የምታጠባውን ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ወይስ ለወለደችው ልጅ አትራራምን? እርስዋ እንኳ ብትረሳ እኔ ግን እናንተን አልረሳም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “በውኑ ሴት፥ ልጅ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ከማ​ኅ​ፀ​ንዋ ለተ​ወ​ለ​ደ​ውስ አት​ራ​ራ​ምን? ሴት ይህን ብት​ረሳ፥ እኔ አን​ቺን አል​ረ​ሳ​ሽም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 49:15
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማኅፀን ትረሳዋለች፥ ትልም በደስታ ይጠባዋል፥ ዳግመኛም የሚያስታውሰው የለም፥ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።”


አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥


አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ ጌታ ግን ተቀበለኝ።


ለዘለዓለምስ ርኅራኄው ተቈረጠችን? የሰጠውስ ቃል ኪዳን ለዘመናት አልቆአልን?


ልጄ ሆይ፥ ምንድነው? የሆዴ ልጅ ሆይ፥ ምንድነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ፥ ምንድነው?


ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።


ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ አገልጋዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ አንተም አገልጋዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ያልተረሳህ ትሆናለህ።


ጽዮን ግን፦ “ጌታ ትቶኛል፥ እርሱ ረስቶኛል” አለች።


ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል የሚራራልሽ ጌታ።


በእውነት ኤፍሬም የተወደደ ልጄ ነውን? ወይስ ደስ የምሰኝበት ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አሁንም ድረስ በትክክል አስታውሰዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል ጌታ።


ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፥ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ ዘንድ አልተተዉም።


ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኗቸው።


ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች።


እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።


የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።


እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ እኔ በምሠራበት ቀን፥ ሰው የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።


እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ነገርን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!


የማያስተውሉ፥ የማይታመኑ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት የሌላቸው ናቸው፤


ጌታ የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ጌታ ሕዝቡን አይተውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች