ኢሳይያስ 46:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል፤ በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፤ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 አንሥተው በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ እቦታው ያደርጉታል፤ በዚያም ይቆማል፤ ከዚያም ቦታ አይንቀሳቀስም፤ ማንም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይመልስም፤ ከጭንቀቱም አያድነውም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 አንሥተውም በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ በአንድ ቦታም ሲያኖሩት በዚያው ይቆማል፤ ካለበት ስፍራም መንቀሳቀስ አይችልም። ማንም ሰው ወደ እርሱ ቢጸልይ መልስ አይሰጠውም፤ ወይም ማንንም ከጥፋት ሊያድን አይችልም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በጫንቃቸው ላይ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ በስፍራውም በአኖሩት ጊዜ በዚያ ይቆማል፤ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይሰማውም፤ ከክፉም አያድነውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፥ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፥ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም። ምዕራፉን ተመልከት |