Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 43:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይልቅስ የማደርገውን አዲስ ነገር ተመልከቱ፤ እርሱም በመፈጸም ላይ ስለ ሆነ ልታዩት ትችላላችሁ፤ በበረሓ መንገድን አወጣለሁ፤ በምድረ በዳም ወንዞችን አፈልቃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነሆ፥ አዲስ ነገ​ርን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እር​ሱም አሁን ይበ​ቅ​ላል፤ እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ በም​ድረ በዳም መን​ገ​ድን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን አደ​ር​ጋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፥ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 43:19
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈለቀ፥ ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ፥


አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።


እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ከእርሱ ውኃ ይወጣል፥ ሕዝቡም ከእርሱ ይጠጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።


በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ፥ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይወርዳሉ።


ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፥ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፥ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።


ጌታ ግን በእነዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ በግርማ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፤ ታላላቅ መርከቦች አያልፉባትም።


ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፥ በረሃውም ሐሤት ያደርጋል፥ እንደ ጽጌረዳም ይፈካል።


በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆዎችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ ማከማቻ፥ የጥማትንም ምድር ለውሃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።


በምድረ በዳ፤ ዝግባን፤ ግራርን፤ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሃ፤ ጥድን፤ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ።


እነሆ፥ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፥ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም ሳይበቅል እርሱን አስታውቃችኋለሁ።


ስለዚህ፥ አንተ፦ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፥ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር፥ ከመሆኑም በፊት አሳይቼህ ነበር።


ሰምተሃል፤ አሁን ይህን ሁሉ ተመልከት፤ ይሄን ራስህ አትመሰክርም? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲስ ነገሮችን ከአሁን ጀምሬ አሳይችኋለሁ።


የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ የበረኅ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።


ጌታም ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርሷም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔድን በረሀዋንም እንደ ጌታ ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።


“ስለዚህ፥ እነሆ፦ ‘የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለው ዳግመኛ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤


አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ታመነቻለሽ? ጌታ በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሴት ወንድን ትከብባለች።”


በልቅሶ ይወጣሉ፤ እኔንም በመማፀናቸው እየመራሁ እመልሳቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኩሬ ነውና።


ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ።


ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል!


መርዘኛ እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከዓለት ድንጋይም ውኃን ያፈለቀልህን፥


በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። እኔንም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች