Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 37:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ናሳራክ በተባለው አምላኩ ቤተ ጣዖት ገብቶ በመስገድ ላይ ሳለ፣ አድራሜሌክና ሳራሳር የተባሉ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት፤ ከዚያም አምልጠው ወደ አራራት ሸሹ። ልጁ አስራዶንም በምትኩ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ከዕለታት በአንዱ ቀን ኒሰሮክ በሚል ስም በሚጠራው ጣዖት ቤተ መቅደስ ውስጥ በስግደት ላይ እንዳለ ከልጆቹ ሁለቱ በተለይ አድራሜሌክና ሣሬጼር ተብለው የሚጠሩት በሰይፍ ገደሉት፤ እነርሱም ወደ አራራት አምልጠው ሄዱ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ከልጆቹ አንዱ አስራዶን የተባለው ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 በአ​ም​ላ​ኩም በና​ሳ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሳራ​ሳር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፥ ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 37:38
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መርከቢቱም በሰባተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች በአንደኛው ጫፍ ላይ ዐረፈች።


አባቶቼ ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ለማዳን የቻለ ማንስ ነበር፤ እናንተንስ አምላካችሁ ከእጄ ለማዳን የሚችል ይመስላችኋልን?


በሰውም እጅ በተሠሩ በምድር አሕዛብ አማልክት ላይ እንደሚናገሩ መጠን በኢየሩሳሌም አምላክ ላይ ተናገሩ።


ጌታም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን የጦር አዛዦቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ላከ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።


ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች አለቆች ቀርበው፦ “እንደ እናንተ አምላካችሁን እንፈልገዋለን፥ የአሦር ንጉሥ ኤሳርሐዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለእርሱ እንሠዋ ነበርና፥ ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው።


አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ወደ ምድር ተጣልክ!


ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፥ የምድርንም ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተ አንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።


ሕዝቅያስ፥ ጌታ በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም፥ ብሎ በጌታ እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።


ሕዝቅያስ፥ ጌታ ያድነናል ብሎ እንዳያታልላችሁ ተጠንቀቁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት አገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋል?


“ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ የምትታመንበት አምላክ አያታልህ።


እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም ላይ በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት’ ” አላቸው።


በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች