ኢሳይያስ 37:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ስለዚህ የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሏል፥ ደንግጠውም ታውከዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለመለመም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 የሕዝቦቻቸው ኀይል ተሟጥጧል፤ ደንግጠዋል፤ ተዋርደዋልም፤ በሜዳ እንዳሉ ዕፀዋት፣ እንደ ለጋ ቡቃያ፣ በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፣ በእንጭጩ ዋግ እንደ መታው ሆነዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 የሕዝቦቻቸው ኀይል ተዳክሞአል፤ እነርሱም ተስፋ ቈርጠው ዐፍረዋል፤ እንደ ሜዳ አበባ፥ እንደ ለጋ ሣር፥ በጣራ ላይ እንደሚበቅልና ፈጥኖ እንደሚጠወልግ ጓሳ ናቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 እጃቸውንም አዝላለሁ፤ ይደርቃሉም፤ በሰገነት ላይ እንዳለ ደረቅ ሣርም ሳያሸት ዋግ እንደ መታው እህልም ይሆናሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ስለዚህ የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሎአል፥ ደንግጠውም ታውከዋል፥ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለመለመም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል። ምዕራፉን ተመልከት |