ኢሳይያስ 37:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 በመልእክተኞችህ በኩል፣ በጌታ ላይ ብዙ የስድብ ቃል ተናገርህ፤ እንዲህም አልህ፤ ‘በሠረገሎቼ ብዛት፣ የተራሮችንም ከፍታ፣ የሊባኖስንም ጫፍ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥም ዝግባዎችን፣ የተመረጡ ጥዶችን ቈርጫለሁ፤ እጅግ ወደራቁት ከፍታዎች፣ እጅግ ውብ ወደሆኑትም ደኖች ደርሻለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 አገልጋዮችህን ልከህ በጌታ ላይ የስድብ ቃል በመናገር፦ ‘በሠረገሎቼ ብርታት ከፍተኛ የሆኑ የሊባኖስ ተራራዎችን ይዤአለሁ፤ ረጃጅም የሆኑትን የሊባኖስ ዛፎችና የተዋቡ የዝግባ ዛፎችን ቈርጬአለሁ፤ በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ጥቅጥቅ ወዳሉት ደኖች አልፌአለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 አንተም በመልእክተኞችህ በኩል እንዲህ ብለህ እግዚአብሔርን ተገዳደርኸው፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ራስ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥሞቹንም ዝግባዎች፥ የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገባለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 አንተም፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፥ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |