Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 34:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። ሬሳቸውም ይከረፋል፤ ተራሮችም በደማቸው ይርሳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከእነርሱም የተገደሉት ወደ ውጭ ይጣላሉ፤ ሬሳቸው ይከረፋል፤ ተራሮችም ደም በደም ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሬሳቸው የትም ተጥሎ ይበሰብሳል እንጂ አይቀበርም፤ ተራራዎችም በደማቸው ይጥለቀለቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ገ​ደ​ሉት በድ​ና​ቸው ይጣ​ላል፤ የሬ​ሳ​ቸ​ውም ግማት ይሸ​ታል፤ ተራ​ሮ​ቹም ከደ​ማ​ቸው የተ​ነሣ ይር​ሳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። የሬሳቸውም ግማት ይሸታል፥ ተራሮችም ከደማቸው የተነሣ ይርሳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 34:3
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


ጎሽ ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትርሳለች፥ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች።


ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።


አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።”


በዚያም ቀን ጌታ የገደላቸው ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም።


ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ ቁጣዬን በደም ባፈስስባትና ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ ባጠፋ፥


በምድር ላይ እተውሃለሁ፥ ለጥ ባለ ሜዳም እጥልሃለሁ፥ የሰማይ ወፎች ሁሉ በአንተ ላይ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፥ የምድርን አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ።


ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል።


በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍና የበረዶ ድንጋይ፥ እሳትና ዲን በእርሱና በወታደሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉት ብዙ ሕዝቦች ላይ አዘንባለሁ።


በዚያም ቀን በእስራኤል፥ በባሕሩ በምሥራቅ በኩል ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ስለሚቀበሩ፥ የመንገደኞች መተላለፊያ ይዘጋል፤ “የሐሞን-ጎግ ሸለቆ” ተብሎ ይጠራል።


አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።


የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ብዙ ነገር አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።


“በግብጽ እንደነበረው ቸነፈርን በመካከላችሁ ላክሁባችሁ፤ ጉልማሶቻችሁንም በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፤ የሰፈራችሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ አወጣሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።


የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስና እስከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ድረስ የሚርቅ ደም ከመጥመቂያው ወጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች