ኢሳይያስ 34:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የምድረ በዳም አራዊት ከጅቦች ጋር ይገናኛሉ፤ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያም ትኖራለች፤ ለእርሷም ማረፊያ ታገኛለች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋራ ዐብረው ይሆናሉ፤ በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤ የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤ ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 አነሮች ከጅቦች ጋር አብረው ይኖራሉ፤ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ የሌሊት ምትሐቶች በፍርስራሾች መካከል ይኖራሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በዚያም አጋንንትና ጂኖች ይገናኛሉ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጂኖችም በዚያ ይኖራሉ፤ ለራሳቸውም ማረፊያን ያገኛሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የምድረ በዳም አራዊት ከተኵሎች ጋር ይገናኛሉ፥ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፥ ጅንም በዚያም ትኖራለች፥ ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች። ምዕራፉን ተመልከት |