ኢሳይያስ 28:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤ በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤ ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገዳገዱ፤ በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤ በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤ ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ነቢያቱና ካህናቱ እንኳ ሰክረው ይንገዳገዳሉ፤ ብዙ ወይን ጠጅና የሚያሰክርም ጠንካራ መጠጥ ስለ ጠጡ አእምሮአቸው ታውኮ ይሰናከላሉ፤ ነቢያቱ ሰክረው ከመደናበራቸው የተነሣ እግዚአብሔር የገለጠላቸውን ራእይ አያስተውሉም፤ ካህናቱም እጅግ ስለሚሰክሩ ለሚቀርብላቸው ጉዳይ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት አይችሉም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፥ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፥ በራእይ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ። ምዕራፉን ተመልከት |