ኢሳይያስ 24:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በጉድጓድ እንደሚከማቹ እስረኞች በአንድነት ይከማቻሉ፤ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፥ ከብዙ ቀንም በኋላ ይቀጣሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በጕድጓድ ውስጥ እንዳሉ እስረኞች፣ በአንድ ላይ ይታጐራሉ፤ በእስር ቤት ይዘጋባቸዋል፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ለፍርድ ይቀርባሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 እግዚአብሔር ነገሥታትን በአንድነት ሰብስቦ በምድር ውስጥ ባለ እስር ቤት ውስጥ እንዳሉ እስረኞች እንዲኖሩ ያደርጋል፤ ከብዙ ቀኖችም በኋላ ይቀጣቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 እነርሱም ይሰበሰባሉ፤ ተዘግቶባቸውም በግዞት ቤት ይኖራሉ፤ ከብዙ ትውልድም በኋላ ይጐበኛሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ግዞተኞች በጕድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፥ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፥ ከብዙ ቀንም በኋላ ይጎበኛሉ። ምዕራፉን ተመልከት |