ኢሳይያስ 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፥ እያንዳንዷን ትንንሽ ዕቃ፥ ከሲኒ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የቤተ ሰቡ ክብር፣ ልጅና የልጅ ልጅ፣ እንዲሁም ከማሰሮ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 “ነገር ግን ቤተ ዘመዶቹና የሩቅ ዘመዶቹ የሆኑ ሁሉ እንደ ከባድ ሸክም ይሆኑበታል፤ ከሲኒ አንሥቶ እስከ እንስራ ያሉት የቤት ዕቃዎች ሁሉ በኲላብ ላይ እንደሚሰቀሉ እነርሱም በእርሱ ላይ የሚንጠለጠሉ ይሆናሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ፥ ልጆቹንም፥ የልጅ ልጆቹንም፥ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፥ ታናናሹንና ታላላቁን ሁሉ ይሰቅሉበታል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፥ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፥ ታናናሹን ዕቃ ሁሉ ይሰቅሉበታል። ምዕራፉን ተመልከት |