Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህስ፥ በትር የሚያነሳውን እንደ መነቅነቅ ዘንግም እንጨት ያይደለውን እንደ ማንሳት ያህል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 10:15
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቁጣዬ በትር ለሆነ፤ የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!


ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፦ “አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን፦ “አታስተውልም” ይለዋልን?


የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’


ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?


በዚያን ቀን፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ፤ ማለትም በአሦር ንጉሥ፤ የራስና የእግር ጠጉራችሁን እንዲሁም ጢማችሁን ይላጫል።


በገዳይህ ፊትም፦ “እኔ አምላክ ነኝ” ትላለህን? ቢሆንም አንተ በገዳይህ እጅ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች