Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሒታውያን ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ መሆኑ አረጋገጡለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወደ ከተማው በር በመጡት ኬጢያውያንም ሁሉ ፊት የአብርሃም ንብረት መሆኑም ተረጋገጠለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በዚያም ተገኝተው የነበሩት ሒታውያን ሁሉ የአብርሃም ርስት መሆኑን አረጋገጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በኬጢ ልጆ​ችና በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር በሚ​ገቡ ሁሉ ፊት ለአ​ብ​ር​ሃም ርስቱ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሻው በእርሱም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 23:18
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የከነዓን ልጆች በኲሩ ጺዶን፥ ተከታዩ ሔት ይባሉ ነበር፤


ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፥ የኬጢ ሰው ኤፍሮንም የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦


ከዚህም በኋላ ኬብሮን በምትባል፥ ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ፥ በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው፥ ዋሻ ውስጥ አብርሃም ሚስቱን ሣራን ቀበረ።


ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤል፥ ከመምሬ በስተ ምሥራቅ በሒታዊው በጾሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ፥ ማክፌላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት።


ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ፥ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው ነገሩ፦


ከከተማይቱም አደባባይ የሚወጡ ሁሉ ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን “እሺ” አሉ፥ ከከተማይቱ አደባባይ የሚወጡት ወንዶች ሁሉ ተገረዙ።


የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ የፈረሙት ምስክሮች፥ በእስርም ቤት አደባባይ የተቀመጡት አይሁድ ሁሉ እያዩ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።


ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ከዚህ በፊት ቦዔዝ ስለ እርሱ የተናገረው የእርሱ የቅርብ ዘመድ ወደዚያው ቦታ መጣ፤ ቦዔዝም ጠርቶ፦ “ወዳጄ ሆይ! ቀረብ በልና አጠገቤ ተቀመጥ” አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች