ሕዝቅኤል 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከእነዚህም እንደገና ወስደህ በእሳት ውስጥ ትጥላቸዋለህ፥ በእሳትም ታቃጥላቸዋለህ፥ ከእርሱም እሳት ወደ እስራኤል ቤት ሁሉ ትወጣለች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እንደ ገናም ከእነዚህ ጥቂት ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምራቸው፤ አቃጥላቸውም። እሳትም ከዚያ ወጥቶ ወደ እስራኤል ቤት ሁሉ ይሠራጫል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ከእርሱም ላይ እንደገና ጥቂት ቈንጥረህ በእሳት ውስጥ ጣለውና እንዲቃጠል አድርገው፤ ከእርሱም የሚነሣው እሳት ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይደርሳል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከእነርሱም ደግሞ ወስደህ በእሳት ውስጥ ትጥላለህ፤ በእሳትም ታቃጥላቸዋለህ፤ ከእርስዋም እሳት ይወጣል፤ የእስራኤልንም ቤት ሁሉ እንዲህ ትላቸዋለህ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ከእነርሱም ደግሞ ወስደህ በእሳት ውስጥ ትጥላለህ በእሳትም ታቃጥላቸዋለህ፥ ከዚያም በእስራኤል ቤት ሁሉ ላይ እሳት ትወጣለች። ምዕራፉን ተመልከት |