Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በረዶና እሳት ነበረ፥ በበረዶውም መካከል እጅግ ከባድ የሚበርቅ እሳት ነበር፥ በግብጽ ምድር ሁሉ አገር ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ሆኖ አያውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በረዶ ወረደ፤ መብረቅም አብረቀረቀ፤ ግብጽ አገር ከሆነችበት ዘመን አንሥቶ በምድሪቱ ሁሉ እንደዚህ ያለ አስከፊ ማዕበል ሆኖ አያውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔር በዚህና በዚያ ከሚራወጥ የመብረቅ ብልጭልጭታ ጋር ከባድ የበረዶ ዝናብ አወረደ፤ ይህም ዐይነቱ የበረዶ ዝናብ በግብጽ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በረ​ዶም ነበረ፤ በበ​ረ​ዶ​ውም መካ​ከል እሳት ይቃ​ጠል ነበር፤ በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ሕዝብ ከኖ​ረ​በት ጊዜ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን እንደ እርሱ ያል​ሆነ እጅግ ብዙና ጠን​ካራ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በረዶም ነበረ፤ በበረዶውም መካከል እሳት ይቃጠል ነበር፤ በረዶውም በግብፅ አገር ሁሉ ሕዝብ ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ያልሆነ እጅግ ታላቅ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 9:24
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይኸውም ለመከራ ጊዜ ለውጊያና ለጦርነት ቀን የጠበቅሁት ነው።


ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ በምድራቸውም የእሳት ነበልባል ወረደ።


በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።


ቤቶችህም የአገልጋዮችህም ቤቶች ሁሉ የግብጽንም ቤቶች ሁሉ ይሞሉታል፤ አባቶችህ የአባቶችህም አባቶች በምድር ላይ ከተቀመጡበት ቀን ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ እንደ እርሱ ያለ አላዩም።’” ተመልሶም ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።


እነሆ እኔ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ፥ ከተመሠረተች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ከባድ በረዶ አዘንባለሁ።


ሙሴም በትሩን ወደ ሰማያት ዘረጋ፤ ጌታም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፥ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ ጌታም በግብጽ ምድር ላይ በረዶ አዘነበ።


በረዶውም በግብጽ ምድር ሁሉ በሜዳ ያለውን ሁሉ ከሰው እስከ እንስሳ መታ፤ የእርሻን ቡቃያ መታ፥ በረዶውም የአገሩን ዛፍ ሁሉ ሰበረ።


ጌታም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድ ቁጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በበረዶ፥ ጠጠርም ይገልጣል።


እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስ መጣ፥ በዙሪያው ብርሃን ያለው መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበር፥ በእሳቱም መካከል የሚያንጸባርቅ ነገር ነበረ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፥ በቁጣዬም ዶፍ ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ሊያጠፋው ይወርዳል።


በዚያን ጊዜ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ ከእንግዲህ ወዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች