ዘፀአት 38:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በሁለተኛው በኩል በአደባባዩ መግቢያ በዚህና በዚያ ዐሥራ አምስት ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ሦስት ምሰሶዎች እና ሦስት እግሮች ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ከሦስት ምሰሶዎችና ከሦስት መቆሚያዎች ጋራ ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆኑ መጋረጃዎች በአደባባዩ መግቢያ በሌላው በኩል ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እንዲሁም በሌላው በኩል በአደባባዩ ደጅ በዚህና በዚያ ስድስት ሜትር ከስድሳ ሳንቲ ሜትር ርዝመት፥ ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት እግሮች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እንዲሁም በሁለተኛው ወገን በአደባባዩ ደጅ በዚህና በዚያ ዐሥራ አምስት ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ሦስትም ምሰሶዎች፥ ሦስትም እግሮች ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እንዲሁም በሁለተኛው ወገን በአደባባዩ ደጅ በዚህና በዚያ አሥራ አምስት ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጆች፥ ሦስትም ምሰሶች፥ ሦስትም እግሮች ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከት |