Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 33:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ክብሬ ሲያልፍ ዓለቱ ስንጥቅ ውስጥ አስቀምጥሃለሁ፥ እስካልፍ ድረስ በመዳፌ እጋርዳለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ክብሬ በዚያ ሲያልፍ በዐለቱ ስንጥቅ ውስጥ አደርግሃለሁ፤ በዚያም እስከማልፍ ድረስ በእጄ እጋርድሃለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የእኔ ክብር በዚያ ሲያልፍ በአለቱ ስንጣቂ አቈይሃለሁ፤ እስካልፍ ድረስ በእጄ እጋርድሃለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ክብ​ሬም በአ​ለፈ ጊዜ በአ​ለቱ ስን​ጥቅ ውስጥ አኖ​ር​ሃ​ለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዓለት አኖርሃለሁ፥ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 33:22
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እዚያም እንደ ደረሰ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ እዚያ ዐደረ። በድንገትም ጌታ “ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ?” ሲል ጠየቀው።


እንዲህም አለ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።


በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።


በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥ ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።


በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በጐልማሶች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው።


ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።


ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፥ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፥ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።


አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፥ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፥ በሰገባውም ውስጥ ሸሽጎኛል።


ሰማያትን እንድዘረጋ ምድርንም እንድመሠርት፥ ጽዮንንም፦ “አንቺ ሕዝቤ ነሽ” እንድል ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፥ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።


ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዐለት ነበር፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።


ይህ እግዚአብሔር የሰዎችን በደል ሳይቆጥርባቸው በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር አስታርቋል፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኑሯል።


ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ “በጌታ የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ ቀኑን ሁሉ ይጠብቀዋል፤ በትከሻዎቹም መካከል ያርፋል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች