Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 32:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሙሴ በሰፈሩ ደጅ ቆሞ፦ “የጌታ ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ!” አለ፤ የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ስለዚህ በሰፈሩ መግቢያ ላይ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ ሌዋውያኑም ሁሉ ከርሱ ጋራ ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለዚህ በሰፈሩ ደጃፍ ቆሞ “የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ!” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፤ ሌዋውያንም ሁሉ በዙሪያው ተሰበሰቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሙሴ በሰ​ፈሩ ደጅ ቆሞ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በሰፈሩ ደጅ ቆሞ፦ የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ! አለ፤ የሌዊም ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 32:26
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአማሳይ ሬሳ አጠገብ ከቆሙት ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ፤ “ኢዮአብን የሚወድ፥ የዳዊትም የሆነ ሁሉ ኢዮአብን ይከተል!” አለ።


ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው?” ሲል ጮኸ፤ ቁጥራቸው ከሁለት እስከ ሦስት የሆነ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ብቅ ብለው ወደ እርሱ ተመለከቱ፤


በክፉዎች ላይ ለእኔ የሚነሣ ማን ነው? ዓመፅንስ በሚያደርጉ ላይ ለእኔ የሚከራከር ማን ነው?


ሙሴ በጠላቶቻቸው ፊት መሳለቂያ እንዲሆኑ አሮን ስድ ለቅቋቸዋልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለቀቁ ባየ ጊዜ፥


እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዱ ሰው ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ወዲህ ወዲያ ተመላለሱ፥ ሰው ሁሉ ወንድሙን፥ ሰው ሁሉ ወዳጁን፥ ሰው ሁሉ ጎረቤቱን ይግደል’”


ከእኔ ጋር ያልሆነ ተቃዋሚዬ ነው፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብ ደግሞ ይበትናል።


ለአንት ሲል እናቱንና አባቱን፥ ‘አላየሁም’ ላለ፥ ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ ልጆቹንም ላላወቀ፥ ቃልህን ላከበረ፥ ቃል ኪዳንህንም ለጠበቀ።


እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “አንተ ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን?” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች