ዘፀአት 31:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ፤ የሚያረክሰው ፈጽሞ ይገደል፥ በእርሷ ሥራን የሚሠራ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 “ ‘ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን አክብሩ፤ ማንም ቢያረክሰው በሞት ይቀጣል፤ በዚያ ቀን ማንም የሚሠራ ቢኖር ከወገኑ ተነጥሎ ይለይ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የተቀደሰ ስለ ሆነ ሰንበትን የዕረፍት ቀን አድርጋችሁ ጠብቁት፤ ይህን የሰንበት ቀን የማይጠብቅና የሥራ ቀን አድርጎ የሚጠቀምበት ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ለእናንተ በእግዚአብሔር የተቀደሰች ናትና ሰንበቴን ጠብቁ፤ የሚያረክሳትም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፤ ሥራንም በእርስዋ የሠራ ሰው ሁሉ ያች ነፍስ ከሕዝብዋ መካከል ተለይታ ትጥፋ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ፤ የሚያረክሰውም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፥ ሥራንም በእርሱ የሠራ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። ምዕራፉን ተመልከት |