ዘፀአት 30:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታደቀዋለህም፥ ከእርሱም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። ለእናንተም ፍጹም ቅዱስ ይሆንላችኋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ከርሱም ጥቂቱን ወቅጠህ ዱቄት በማድረግ አልመህ በመገናኛው ድንኳን ከምስክሩ ፊት ለፊት ከአንተ ጋራ በምገናኝበት ስፍራ አስቀምጠው፤ ለአንተ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ከእርሱም ጥቂቱን ወስደህ በመውቀጥ ካላምከው በኋላ ወደ ድንኳኑ ወስደህ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እርጨው፤ ይህንንም ዕጣን ፍጹም የተቀደሰ እንዲሆን አድርግ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፤ ታልመውማለህ፤ ከዚያም ለአንተ በምገለጥበት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሁንላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታልመውማለህ፤ ከዚያም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም የቅዱሳን ቅዱስ ይሁንላችሁ። ምዕራፉን ተመልከት |