Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 28:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በላዩ ያለው በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ መታጠቂያ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በጥበብ የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ከኤፉድ ጋራ አንድ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ኤፉዱ ከተሠራባቸው ተመሳሳይ ነገሮች በብልኀት የተጠለፈ መታጠቂያ አንድ ላይ እንደ ተሠራ ሆኖ ከኤፉዱ ጋር ይጣበቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በላ​ዩም የተ​ጠ​ለ​ፈው የል​ብሰ መት​ከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ፥ ከጥሩ በፍ​ታም የተ​ሠራ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉድ ቍድ እንደ እርሱ ከእርሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም የተሠራ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 28:8
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁለቱ ወገን አንድ ሆኖ እንዲጋጠም በሁለቱ ትከሻ ላይ የሚጋጠም ይሁን።


ሁለት የመረግድ ድንጋይ ወስደህ የእስራኤልን ልጆች ስም ቅረጽባቸው፤


ልብሶቹን ወስደህ ለአሮን እጀ ጠባቡን፥ የኤፉዱን መደረቢያ፥ ኤፉዱንና የደረት ኪስ ታለብሰዋለህ፥ በብልሃትም የተጠለፈ ኤፉድ ታስታጥቀዋለህ፤


በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቋድ እንደ እርሱ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ፥ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር።


ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፤ ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።


ልብስም አለበሰው፥ በመርገፍም በተጌጠ ዝናር አስታጠቀው፥ ቀሚስም አለበሰው፥ ኤፉድም ደረበለት፥ በብልሃትም በተጠለፈ የኤፉድ ማንጠልጠያ አስታጠቀውና በእርሱ ላይ ኤፉዱን አሰረው።


ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች