Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 28:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 በመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ፈትል በመጠምጠሚያው ላይ ስፋው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ከመጠምጠሚያው ጋራ እንዲያያዝ ሰማያዊ ፈትል እሰርበት፤ እርሱም በመጠምጠሚያው ፊት በኩል ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 በመጠምጠሚያውም ፊት በሰማያዊ ድሪ እንዲንጠለጠል አድርግ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 በሰ​ማ​ያ​ዊም ፈትል በመ​ጠ​ም​ጠ​ሚ​ያው ላይ በስ​ተ​ፊቱ ታን​ጠ​ለ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 በሰማያዊም ፈትል በመጠምጠሚያው ፊት ላይ ታንጠለጥለዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 28:37
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የደረት ኪሱም በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረት ኪሱን ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል።


“የኤፉዱን መደረቢያ ሙሉ ሰማያዊ አድርገው።


ከንጹህ ወርቅ ቅጠል ሥራ፥ በእርሱም ላይ እንደ ማኅተም ቅርጽ ‘ለጌታ የተቀደሰ’ የሚል ቅረጽበት።


በአሮን ግምባር ላይ ይሆናል፥ አሮንም የእስራኤል ልጆች በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱስ ስጦታቸው ሁሉ ላይ ያለውን ኃጢአት ይሸከም፤ በጌታ ፊት ሞገስ እንዲሆንላቸው ቅጠሉ ሁልጊዜ በግምባሩ ላይ ይሁን።


የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ፥ ኤፉድ፥ ቀሚስ፥ የተጠለፈ እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያና መታጠቂያ፤ ካህን እንዲሆንልኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ የተቀደሰ ልብስ ይሥሩላቸው።


መጠምጠሚያውን በራሱ ላይ ታደርጋለህ፥ የተቀደሰውንም አክሊል በመጠምጠሚያው ላይ ታኖራለህ።


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል፥ የወርቅ ጉንጉን ሆኖ በቅጠል መልክ የተሠራውን የተቀደሰ አክሊል፥ አደረገ።


ከዚያም፥ “ንጹሕ የራስ ላይ ጥምጣም ያድርጉለት” አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፤ የጌታም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ እንዲያደርጉ፥ በዘርፉም ጫፍ ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል እንዲያኖሩበት እዘዛቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች