Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 28:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በተጨማሪም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ በኤፉዱም ፊት ለፊት ከትከሻዎቹ በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ በመያዣው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶች አበጅተህ ከኤፉዱ መታጠቂያ ከፍ ብሎ ከመጋጠሚያው አጠገብ ካለው በኤፉዱ ፊት ለፊት፣ በትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ግርጌ ጋራ አያይዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከነዚህም ሌላ ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ ከፊት ለፊት በኩል በትከሻ ላይ ከሚወርዱት ከኤፉዱ ማንገቻዎች ጋር ከታች በኩል ታያይዘዋለህ፤ መያያዝ ያለበትም በስፌቱ መጋጠሚያ አጠገብና በብልኀት ከተጠለፈው መታጠቂያ በላይ በኩል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ደግ​ሞም ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሥራ፤ በል​ብሰ መት​ከፉ ፊት ከጫ​ን​ቃ​ዎች በታች በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ከፉ ቋድ በላይ በመ​ጋ​ጠ​ሚ​ያው አጠ​ገብ ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ በኤፉዱም ፊት ከጫንቃዎች በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቍድ በላይ በመያዣው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 28:27
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረት ኪሱ በሁለቱ ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ።


የደረት ኪሱም በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረት ኪሱን ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል።


በላዩ ያለው በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ መታጠቂያ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ ይሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች