ዘፀአት 23:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 መፈራቴን በፊትህ እልካለሁ፥ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደንግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 “በሚያጋጥሙህ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስፈራቴን በፊትህ እልካለሁ፤ ግራም አጋባቸዋለሁ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ወደ ኋላ ተመልሰው እንዲሸሹ አደርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 “አንተን የሚቃወሙህ ሁሉ እኔን እንዲፈሩ አደርጋለሁ፤ በአንተ ላይ ጦርነት በሚያስነሡ ሕዝቦች ላይ ሁከት አመጣለሁ፤ ጠላቶችህ ወደ ኋላ ተመልሰው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 በፊትህ መፈራትን እሰድዳለሁ፤ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ እንዲሸሹልህ አደርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 መፈራቴንም በፊትህ እሰድዳለሁ፥ የምትሄድበትንም ሕዝብ ሁሉ አስደንግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |