ዘፀአት 21:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 የአንድ ሰው በሬ የሌላውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞትም፥ በሕይወት ያለውን በሬ ይሽጡ፥ ዋጋውንም እኩል ይካፈሉት፤ የሞተውንም ደግሞ እኩል ይካፈሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም35 “የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድለው፣ በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው ገንዘቡንና የሞተውን እንስሳ እኩል ይካፈሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድል ሁለቱ ሰዎች በሕይወት ያለውን በሬ ሸጠው ገንዘቡን ለሁለት ይካፈሉት፤ የሞተውንም በሬ ሥጋ ለሁለት ይካፈሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 “የሰው በሬ የሌላውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞትም፥ ደኅናውን በሬ ይሽጡ፤ ዋጋውንም በትክክል ይካፈሉ፤ የሞተውንም ደግሞ በትክክል ይካፈሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 የሰው በሬ የሌላውን በሬ እስኪሞት ድረስ ቢወጋ፥ ደኅናውን በሬ ይሽጡ፥ ዋጋውንም በትክክል ይካፈሉ፤ የሞተውንም ደግሞ በትክክል ይካፈሉ። ምዕራፉን ተመልከት |