ዘፀአት 16:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 እንዲህም ሆነ በስድስተኛው ቀን ሁለት እጥፍ አድርገው ሁለት ዖሜር ምግብ ለአንድ ሰው ሰበሰቡ፤ የማኅበሩም መሪዎች ሁሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በስድስተኛው ቀን ለእያንዳንዱ ሰው ሁለት ሁለት ጎሞር አድርገው ዕጥፍ ሰበሰቡ፤ የማኅበሩም አለቆች ወደ ሙሴ መጥተው ይህንኑ ነገሩት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 በስድስተኛው ቀን ለእያንዳንዱ ሦስት ኪሎ ይሰበስቡ ነበር፤ የማኅበሩ መሪዎች ሁሉ መጥተው ስለ ምግቡ ለሙሴ ነገሩት፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 እንዲህም ሆነ፤ በስድስተኛው ቀን ሁለት እጥፍ አድርገው እያንዳንዳቸው ሁለት ጎሞር እንጀራ ሰበሰቡ፤ የማኅበሩም አለቆች ሁሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 እንዲህም ሆነ፤ በስድስተኛው ቀን ሁለት እጥፍ አድርገው እያንዳንዳቸው ሁለት ጎሞር እንጀራ ለቀሙ፤ የማኀበሩም አለቆች ሁሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት። ምዕራፉን ተመልከት |