Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 25:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እኔም ‘ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፥ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም፤’ ብዬ መለስሁላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “እኔም፣ ተከሳሽ በከሳሾቹ ፊት ቆሞ ለተከሰሰበት ነገር መልስ ለመስጠት ዕድል ሳያገኝ፣ አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ እንዳልሆነ ነገርኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔ ግን ‘ተከሳሽ ከከሳሾች ፊት ቆሞ ለተከሰሰበት ነገር የመከላከያ መልስ ሳይሰጥ ተከሳሹን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም’ ብዬ መለስኩላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እኔም፦ ተከ​ሳሹ በከ​ሳ​ሾቹ ፊት ሳይ​ቆም፥ ለተ​ከ​ሰ​ሰ​በ​ትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያ​ገኝ ማንም ቢሆን አሳ​ልፎ መስ​ጠት የሮ​ማ​ው​ያን ሕግ አይ​ደ​ለም ብየ መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እኔም፦ “ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፥ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም” ብዬ መለስሁላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 25:16
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታውም “ባርያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ፥ ተቈጣ።


ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።


ወደ ፍርድ አስቀድሞ የገባ ጻድቅ ይመስላል፥ ባልንጀራው ግን መጥቶ ይመረምረዋል።


ወደ ምኵራቦች፥ ወደ ገዢዎችና ወደ ባለ ሥልጣኖች ሲጐትቱአችሁ፥ እንዴት ወይም ምን እንደምትመልሱ ወይም እንደምትናገሩ አትጨነቁ፤


“ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ፥ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?”


በዚህም ሰው አይሁድ ሤራ እንደሚያደርጉበት ባመለከቱኝ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ አንተ ላኩት፤ ከሳሾቹንም ደግሞ በፊትህ እንዳይከሱት ዘንድ አዘዝኋቸው።


“ከሳሾችህ ደግሞ ሲመጡ እሰማሃለሁ፤” አለው፤ በሄሮድስም ግቢ ውስጥ ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ።


አግሪጳም ጳውሎስን “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል፤” አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል መለሰ፦


አንተም ይህ መደረጉን ብትሰማ፥ ነገሩን በጥንቃቄ መርምር፤ የተባለውም እውነት ከሆነና እንዲህ ያለው አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ዘንድ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች