ሐዋርያት ሥራ 25:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ጳውሎስ ግን “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሣር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “አሁንም ቢሆን ፍትሕ ማግኘት በምችልበት፣ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ምንም በደል አልፈጸምሁም፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ጳውሎስ ግን እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “እነሆ! እኔ ልፋረድበት በሚገባኝ በሮም ንጉሠ ነገሥት የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተም በደንብ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ጳውሎስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀርባለሁ፤ ፍርዴም በዚያ ሊታይልኝ ይገባል፤ በአይሁድም ላይ የበደልሁት በደል እንደሌለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታውቃለህ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ጳውሎስ ግን፦ “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም። ምዕራፉን ተመልከት |