Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 21:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ጳውሎስ ግን “እኔስ አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው የጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር ነኝ፤ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ጳውሎስም፣ “እኔስ በኪልቅያ ያለችው የታዋቂዋ የጠርሴስ ከተማ ነዋሪ የሆንሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ ለሕዝቡ ንግግር እንዳደርግ ፍቀድልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ጳውሎስም “እኔ በኪልቅያ በምትገኘውና ዝነኛ በሆነችው በጠርሴስ ከተማ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ እባክህ ለሕዝቡ እንድናገር ፍቀድልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔስ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባ​ትም ሀገር ጠር​ሴስ የታ​ወ​ቀች የቂ​ል​ቅያ ከተማ ናት፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ቸው ትፈ​ቅ​ድ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ጳውሎስ ግን፦ እኔስ አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው የጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር ነኝ፤ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 21:39
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ “ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።


አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።


ጳውሎስ ግን “እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም፤ ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን፤” አላቸው።


ወደ ሰፈርም ሊያገቡት በቀረቡ ጊዜ፥ ጳውሎስ የሻለቃውን “አንድ ነገር ብነግርህ ትፈቅዳለህን?” አለው። እርሱም “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን?


“እኔ የኪልቅያ በምትሆን በጠርሴስ የተወለድሁ፥ በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ።


ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ባሰቡ ጊዜ ከጭፍሮቹ ጋር ደርሼ አዳንሁት፤ ሮማዊ እንደሆነ አውቄ ነበርና።


ካነበበውም በኋላ የወዴት አውራጃ እንደሆነ ጠየቀው፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑንም ባወቀ ጊዜ


የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና በእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤


ጌታም “ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤


ወንድሞችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ወሰዱት፤ ወደ ጠርሴስም ሰደዱት።


ነገር ግን ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተም ስላለች ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች