2 ነገሥት 18:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቆስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል፣ የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቈስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብፅ ትታመናለህ፤ ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል፥ ያቈስለውማል፤ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብጽ ትታመናለህ፤ ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል፤ ያቈስለውማል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።’ ምዕራፉን ተመልከት |