2 ዜና መዋዕል 7:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 መልሰውም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ሰዎቹም መልሰው፣ ‘አዎን እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ጥፋት ያመጣባቸው አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎች አማልክትን በመከተል ስላመለኳቸውና ስላገለገሏቸው ነው’ ይላሉ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ሰዎችም ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ጥፋት በእነርሱ ላይ ያደረሰባቸው ከግብጽ ያወጣቸውን የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉና ስለ ሰገዱላቸው ነው’ ሲሉ ይመልሱላቸዋል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 መልሰውም፦ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን ያባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለ አገለገሏቸውም፥ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው” ይላሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 መልሰውም ‘ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው፤’ ይላሉ።” ምዕራፉን ተመልከት |