2 ዜና መዋዕል 34:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የካህናቶቻቸውንም አጥንት በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ፤ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የካህናቱን ዐጥንት በመሠዊያዎቻቸው ላይ አቃጠለ፤ በዚህ ዐይነትም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ኢዮስያስ የአሕዛብን ካህናት ዐፅም ሁሉ እነርሱ ራሳቸው ይሰግዱላቸው በነበሩት መሠዊያዎች ላይ አቃጠላቸው፤ ይህን ሁሉ በማድረጉም ይሁዳና ኢየሩሳሌም በሥርዓት እንደገና እንዲነጹ አደረገ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የካህኖቻቸውንም አጥንት በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ። ይሁዳንና ኢየሩሳሌምንም አነጻ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የካህናቶቻቸውንም አጥንት በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ፤ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። ምዕራፉን ተመልከት |
ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፥ በኰረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮችን አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን ዐፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም ዓይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፤ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህን ትንቢት ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር አይቶ፥