Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 32:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንዲሁም ጌታ ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔርም ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬምና ከሌሎችም እጅ ሁሉ አዳናቸው፤ በዙሪያቸው ካሉትም ሁሉ ጠበቃቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር ንጉሥ ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ከሰናክሬብና ከሌሎቹም ጠላቶቻቸው እጅ በመታደግ አዳናቸው፤ ጐረቤቶቻቸው ከሆኑትም ሕዝቦች ሁሉ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ፈቀደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ከአ​ሦር ንጉሥ ከስ​ና​ክ​ሬም እጅና ከሁ​ሉም እጅ አዳ​ና​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ካለው ሁሉ አሳ​ረ​ፋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከሁሉም እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 32:22
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በይሁዳ ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ወደ መሬት ሥር ሰድዶ እንደሚያድግና እንደሚያፈራ ተክል ይሆናሉ፤


ጌታም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን የጦር አዛዦቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ላከ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።


ለነገሥታት መድኃኒትን የሚሰጥ፥ ባርያውን ዳዊትን ከክፉ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።


በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።


በአንተ ምክር መራኸኝ፥ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።


ጌታ ፈራጃችን ነው፥ ጌታ ሕግን ሰጪያችን ነው፥ ጌታ ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።


ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።


ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፤ እነርሱንም በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በጌታ አድናቸዋለሁ።”


የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።


ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ትዕግሥት ልባችሁን ያቅናው።


በዚያ ቀን ጌታ እስራኤልን ታደገው፤ ጦርነቱም ከቤትአዌን ዘልቆ ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች