2 ዜና መዋዕል 30:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ከካህናቱም እጅግ ብዙ ተቀድሰው ነበርና ጉባኤው ሁሉ እንደገና ሰባት ቀን በዓሉን ለማክበር ተማከሩ፤ በደስታም እንደገና ሰባት ቀን በዓሉን አከበሩ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ጉባኤውም ሁሉ በተከታዩ ሰባት ቀን በዓሉን እንደ ገና ለማክበር ተስማሙ፣ ስለዚህ በዓሉን ለሰባት ተጨማሪ ቀን በታላቅ ደስታ አከበሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 በተጨማሪ ለሰባት ቀን በዓል እንዲያደርጉ በአንድነት ወስነው በዓሉን በደስታ አከበሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ጉባኤው ሁሉ እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል ያደርጉ ዘንድ ተማከሩ፤ በደስታም እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23-24 የይሁዳም ንጉሥ ሕዝቅያስ ስለ ቍርባን ሺህ ወይፈኖችና ሰባት ሺህ በጎች ለጉባኤው ሰጥቶ ነበርና፥ አለቆቹም ሺህ ወይፈኖችና አሥር ሺህ በጎች ለጉባኤው ሰጥተው ነበርና፥ ከካህናቱም እጅግ ብዙ ተቀድሰው ነበርና ጉባኤው ሁሉ እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል ያደርጉ ዘንድ ተማከሩ፤ በደስታም እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከት |