2 ዜና መዋዕል 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 የኪሩቤልም ክንፎች ሀያ ክንድ ሙሉ ተዘርግተው ነበር፤ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፥ የቤቱንም ግንብ ይነካ ነበረ፤ ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፥ የሁለተኛውንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ ዐምስት ክንድ ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው ዐምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11-13 ኪሩቤል በቅድስተ ቅዱሳን መግቢያ ትይዩ ጐን ለጐን ቆመው ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብም ሁለት ክንፎች ነበሩት፤ የእያንዳንዱም ክንፍ ርዝመት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ነበር፤ ሁለቱ ክንፎች በየአቅጣጫው የተዘረጉ ሆነው በክፍሉ መኻል ላይ እርስ በርሳቸው ይነካካሉ፤ ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ እያንዳንዱ በየአቅጣጫው ያለውን ግድግዳ የሚነካ ሲሆን፥ የእነዚህ የተዘረጉ ክንፎች ጠቅላላ ወርድ ዘጠኝ ሜትር ያኽል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 የኪሩቤልም ክንፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘርግተው ነበር፤ የአንዱ የኪሩብ ክንፍ ርዝመት አምስት ክንድ ነበረ፤ የቤቱንም ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁለተኛውም ክንፍ ርዝመት አምስት ክንድ ነበረ፤ የሁለተኛውንም ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 የኪሩቤልም ክንፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘርግተው ነበር፤ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ የቤቱንም ግንብ ይነካ ነበረ፤ ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ምዕራፉን ተመልከት |