2 ዜና መዋዕል 29:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ንጉሡም የሚቃጠል መሥዋዕትና የኃጢአት መሥዋዕት ለእስራኤል ሁሉ እንዲደረግ አዝዞ ነበርና ለእስራኤል ሁሉ ማስተሰረያ እንዲያደርጉ የኃጢአቱን መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ላይ አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ንጉሡ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኀጢአት መሥዋዕት ስለ እስራኤል ሁሉ እንዲቀርብ አዝዞ ስለ ነበር፣ ካህናቱ ፍየሎቹን ዐርደው ስለ እስራኤል ሁሉ ማስተስረያ እንዲሆን የኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ ደሙን በመሠዊያው ላይ አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ንጉሡ ስለ መላው የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕትና ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብ አዞ ስለ ነበር፥ ካህናቱ በትእዛዙ መሠረት ፍየሎቹን ዐርደው ደማቸውን መሥዋዕት በማድረግ በመሠዊያው ላይ አፈሰሱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ካህናቱም አረዱአቸው፤ ንጉሡም የሚቃጠል መሥዋዕትና የኀጢአት መሥዋዕት ለእስራኤል ሁሉ እንዲደረግ አዝዞ ነበርና ለእስራኤል ሁሉ ማስተስረያ ያደርጉ ዘንድ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ንጉሡም የሚቃጠል መሥዋዕትና የኃጢያት መሥዋዕት ለእስራኤል ሁሉ እንዲደረግ አዝዞ ነበርና ለእስራኤል ሁሉ ማስተሰረያ ያደርጉ ዘንድ የኃጢያቱን መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ላይ አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከት |