2 ዜና መዋዕል 28:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ስለዚህ ጌታ አምላኩ በሶርያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ ሶሪያውያንም ድል አደረጉት፥ ከእርሱም ብዙ ምርኮኞች ወስደው ወደ ደማስቆ አመጡ። ደግሞም በእስራኤል ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም በታላቅ ውግያ ድል አደረገው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ስለዚህ አምላኩ እግዚአብሔር ለሶርያ ንጉሥ አሳልፎ ሰጠው፤ ሶርያውያንም ድል አደረጉት፤ ከሕዝቡም ብዙዎቹን ምርኮኞች አድርገው ወደ ደማስቆ ወሰዷቸው። ደግሞም ለእስራኤል ንጉሥ ዐልፎ ተሰጠ፤ እርሱም ከባድ ጕዳት አደረሰበት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5-6 ንጉሥ አካዝ ኃጢአት ስለ ሠራ የሶርያ ንጉሥ ድል እንዲያደርገውና ብዙ ወገኖቹን እስረኞች አድርጎ ወደ ደማስቆ እንዲወስድ እግዚአብሔር ፈቀደ፤ እንዲሁም የረማልያ ልጅ የሆነው የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ አካዝን ድል እንዲያደርግና እጅግ በጣም ጀግኖች ከሆኑ ከይሁዳ ወታደሮች መካከል በአንድ ቀን መቶ ኻያ ሺህ እንዲገድል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ይህን የፈቀደበት ምክንያት የይሁዳ ሰዎች እርሱን ስለ ተዉ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ስለዚህ አምላኩ እግዚአብሔር በሶርያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም መታው፤ ከእርሱም ብዙ ምርኮኞችን ወሰደ፤ ወደ ደማስቆም አመጣው። ደግሞም በእስራኤል ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም በታላቅ አመታት መታው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ስለዚህ አምላኩ እግዚአብሔር በሶርያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ ሶሪያውያንም መቱት፤ ከእርሱም ብዙ ምርኮኞች ወስደው ወደ ደማስቆ አመጡ። ደግሞም በእስራኤል ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም በታላቅ አመታት መታው። ምዕራፉን ተመልከት |