2 ዜና መዋዕል 26:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ዖዝያንም ተቈጣ፤ የሚያጥንበትም ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በጌታ ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግምባሩ ላይ ለምጽ ታየ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ጥና በእጁ ይዞ ዕጣን ለማጠን ዝግጁ የነበረው ዖዝያን ተቈጣ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው ፊት ሆኖ ካህናቱ ላይ እየተቈጣ ሳለ፣ በግንባሩ ላይ የቈዳ በሽታ ወጣበት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ዕጣን ለማጠን ዝግጁ ሆኖ ጥናውን በእጁ እንደ ያዘ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው አጠገብ ቆሞ የነበረው ዖዝያም በካህናቱ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ወዲያውኑ በግንባሩ ላይ የቆዳ በሽታ ታየ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ዖዝያንም ተቈጣ፤ በመቅደስም የሚያጥንበት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግንባሩ ላይ ለምጽ ታየ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ዖዝያንም ተቍጣ፤ የሚያጥንበትም ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቍጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግምባሩ ላይ ለምጽ ታየ። ምዕራፉን ተመልከት |