2 ዜና መዋዕል 26:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚቀመጡትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች ሠራ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ አገር ድረስ ተሰማ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 በኢየሩሳሌምም፣ ንድፎቻቸው በባለሙያዎች የተዘጋጁ፣ በመጠበቂያ የግንብ ማማዎችና በየማእዘኑ መከላከያዎች ላይ ፍላጻ የሚስፈነጠርባቸውንና ትልልቅ ድንጋዮች የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አሠራ። እስኪበረታም ድረስ በሚያስደንቅ ሁኔታ ስለ ታገዘ፣ ዝናው በርቀትና በስፋት ተሰማ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ንጉሥ ዖዝያ በኢየሩሳሌም በእጅ ሥራ ጥበብ የሠለጠኑ ሰዎች ከመጠበቂያ ግንቦችና ከከተማይቱ ቅጽር ማእዘኖች ላይ ፍላጻዎችንና ታላላቅ ድንጋዮችን የሚያስፈነጥሩ መሣሪያዎችን እንዲሠሩ አደረገ፤ እግዚአብሔር ስለ ረዳውም እጅግ በረታ፤ እጅግም ገናና ሆነ፤ ዝናውም በሁሉ ስፍራ ተሰማ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን ፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና የመሣሪያዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ። ምዕራፉን ተመልከት |