2 ዜና መዋዕል 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች፦ “ከሰልፉ መካከል አውጡአት የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑም፦ “በጌታ ቤት ውስጥ አትግደሉአት” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ካህኑ ዮዳሄም የወታደሮች አዛዥ ወደሆኑት ወደ መቶ አለቆቹ፣ “በሰልፉ መካከል አውጥታችሁ አምጧት፤ የሚከተላት ካለም በሰይፍ ግደሉት” ሲል ላከባቸው። ካህኑም፣ “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አትግደሏት” ብሎ ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር መኰንኖቹን ጠርቶ “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርስዋን ከሞት ለማትረፍ የሚሞክር ሰው ቢኖር ግደሉት” ሲል አዘዛቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ካህኑም ኢዮአዳ ወጥቶ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን አለቆችና የመቶ አለቆች፥ “ከቤተ እግዚአብሔር ወደ ውጭ አውጡአት፤ የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑ፥ “በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አትገደል” ብሎአልና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች “ወደ ሰልፉ መካከል አውጡአት የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑም “በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አትግደሉአት” አለ። ምዕራፉን ተመልከት |