2 ዜና መዋዕል 23:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ጎቶሊያም የሚሮጡትንና ንጉሡን የሚያመሰግኑትን የሕዝቡን ድምፅ በሰማች ጊዜ ወደ ሕዝቡ ወደ ጌታ ቤት መጣች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ጎቶልያም የሚሯሯጠውንና ደስታውን ለንጉሡ የሚገልጠውን የሕዝቡን ጩኸት ስትሰማ፣ ሕዝቡ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ዐታልያ ሕዝቡ ለንጉሡ ያደረገውን እልልታና ሆታ ሰምታ ሕዝብ ወደ ተሰበሰበበት ወደ ቤተ መቅደስ በፍጥነት መጣች። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ጎቶልያም የሚሮጡትንና ንጉሡን የሚያመሰግኑትን የሕዝቡን ድምፅ በሰማች ጊዜ ወደ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ቤት መጣች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ጎቶሊያም የሚሮጡትንና ንጉሡን የሚያመሰግኑትን የሕዝቡን ድምጽ በሰማች ጊዜ ወደ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ቤት መጣች። ምዕራፉን ተመልከት |