Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 16:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቶ በተሞላው አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዳዊት ከተማ ከዐለት አስፈልፍሎ ለራሱ ባሠራውም መቃብር ቀበሩት። በቅመማ ቅመምና በልዩ ልዩ ጣፋጭ ሽቱዎች በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፤ ስለ ክብሩም ትልቅ እሳት አነደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሬሳውም በልዩ ቅመማ ቅመምና በሽቶ ታሽቶ እርሱ ራሱ በዳዊት ከተማ ከአለት አስፈልፍሎ ባሠራው መቃብር ተቀበረ፤ ስለ ክብሩም ብዙ እንጨት ከምረው በማንደድ ታላቅ ለቅሶ አደረጉለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ለእ​ር​ሱም ለራሱ በሠ​ራው መቃ​ብር በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ በቀ​ማሚ ብል​ሃት የተ​ሰ​ናዳ ልዩ ልዩ መል​ካም ሽቱ በተ​ሞላ አልጋ ላይም አኖ​ሩት፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የቀ​ብር ሥር​ዐት አደ​ረ​ጉ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቱ በተሞላው አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 16:14
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴፍም አገልጋዮቹ የሆኑትን መድኃኒት ቀማሚዎች የአባቱን ሬሳ መልካም መዓዛ ባለው ሽቶ እያሹ እንዲያደርቁት ትእዛዝ ሰጠ።


አባቴ፦ ‘እነሆ እኔ እሞታለሁ፥ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ’ ሲል አስምሎኛል። አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።”


አሣሄልንም ከወደቀበት አንሥተው በቤተልሔም በሚገኘው በአባቱ መቃብር ቀበሩት። ከዚያም ኢዮአብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሡ አድረው፥ ኬብሮን ንጋት ሆነ።


አሳም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በነገሠም በአርባ አንደኛው ዓመት ሞተ።


ከቀንም ወደ ቀን እንዲህ ሆነ፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀቱ ወጣ፥ በክፉም ደዌ ሞተ። ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርገው እንደ ነበረ ለእርሱ የመቃብር ወግ አላደረገም።


ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ልጆች መቃብር በላይኛው ክፍል ቀበሩት፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ ታላቅ የቀብር ሥርዓት አደረጉለት። ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።


አገልጋዮቹም ከሠረገላው አውርደው ለእርሱ በነበረው በሁለተኛው ሠረገላ ውስጥ አስቀመጡት፥ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጡት፤ እርሱም ሞተ፥ በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌምም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱ።


የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፥ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።


መቃብር በዚህ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ሥፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖሪያ ያሳነጽክ በዚህ ስፍራ ምን መብት አለህ? በዚህስ ለአንተ ወገን የሆነ ማን አለ?


በሰላም ትሞታለህ። ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት እንደ አባቶችህ ዕጣን እንደታጠነላቸው፥ እንዲሁ ለአንተም ዕጣንን ያጥኑልሃል፦ “ወየው! ጌታ ሆይ!” እያሉ ያለቅሱልሃል፤’ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ።”


ሰንበት ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፥ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሄደው የኢየሱስን ሥጋ ለመቀባት ሽቱ ገዙ።


ጀግኖቻቸው ሁሉ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ። የሳኦልንና የልጆቹንም ሬሳ ከግንቡ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ አምጥተው አቃጠሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች