Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 15:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለጌታም በታላቅ ድምፅና በዕልልታ፥ እምቢልታንና ቀንደ መለከትንም እየነፉ ማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ይህንም በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ ለእግዚአብሔር ማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የገቡትን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ መሆናቸውንም በማረጋገጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በእግዚአብሔር ስም ማሉ፤ ከዚህም በኋላ በጥሩምባና በእምቢልታ ድምፅ ታጅበው በሆታና በእልልታ ደስታቸውን ገለጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ድም​ፅና በእ​ል​ልታ፥ በእ​ን​ቢ​ል​ታና በቀ​ንደ መለ​ከት ማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለእግዚአብሔርም በታላቅ ድምፅና በዕልልታ፥ በእምቢልታና በቀንደ መለከት ማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 15:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእስራኤልንም አምላክ ጌታን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ እንዲገደል ማሉ።


በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ ጌታም በዙሪያቸው እረፍት ሰጣቸው።


የቀሩት ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ ከምድር ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉት ሁሉ፥


ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፦ “ይህን ቃል የማይፈጽመውን ሰው እግዚአብሔር ከቤቱና ከንብረቱ እንደዚሁ ያራግፈው፤ እንዲሁም የተራገፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፦ “አሜን” አሉና ጌታን አመሰገኑ፤ ሕዝቡ ቃል ኪዳኑ አደረጉ።


በዋሽንትና በመለከት ድምፅ በንጉሡ በጌታ ፊት እልል በሉ።


ሙሴም መጣ ለሕዝቡም የጌታ ቃሎች ሁሉ ሥርዓቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፦ “ጌታ የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ።


የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ በሕዝቡ ጆሮ ላይ አወጀ፤ እነርሱም፦ “ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም” አሉ።


ሕዝቡም ኢያሱን፦ “ጌታ አምላካችንን እናገለግላለን፥ ድምፁንም እንሰማለን” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች