Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 22:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ወደ እርሱ ተሰባሰቡ፤ እርሱም መሪያቸውም ሆነ። እነርሱም አራት መቶ ያህል ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የተጨነቁ፣ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ አራት መቶ ያህል ሰዎች፣ ወደ እርሱ ተሰባሰቡ፤ መሪያቸውም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸው፥ እንዲሁም ሆድ የባሳቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እርሱ ስለ ሄዱ ብዛታቸው በድምሩ እስከ አራት መቶ ደረሰ፤ ዳዊትም የእነርሱ መሪ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የተጨነቀም ሁሉ፥ ብድርም ያለበት ሁሉ፥ የተከፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተከማቸ እርሱም በላያቸው አለቃ ሆነ፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 22:2
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሑሻይም በተጨማሪ እንዲህ አለው፥ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ጦረኞችና ግልገሎችዋም እንደተነጠቁባት የዱር ድብ አምርረው የሚነሡ መሆኑን ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በጦር ሜዳ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤


እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤


የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባሏ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባርያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።


ለጥፋት ለቀረበው ሰው ብርቱ መጠጥ ስጡት፥ ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት፥


ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ ግፈኞችም በኃይል ይወስዱአታል።


እናንተ ደካሞችና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ፥ ሁሉ ነገር በእርሱና ለእርሱ የተፈጠረው፥ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ ተገብቷልና።


ስለዚህም ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ሸሽቶ መኖሪያውን ጦብ በተባለች ምድር አደረገ፤ እዚያም ወሮበሎች ተሰባስበው ተከተሉት።


የዳን ሰዎች፥ “አትሟገተን፤ ያለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጉዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት።


እርሷም ከልቧ ኀዘን የተነሣ ምርር ብላ እያለቀሰች ወደ ጌታ ጸለየች።


ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ፥ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ለሞዓብ ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ፥ አባቴና እናቴ መጥተው ካንተ ዘንድ እንዲቀመጡ ፈቃድህ ነውን?” አለው።


ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፥ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ።


ዳዊትም ሰዎቹን፥ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋር ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።


ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተማርራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በጌታ በረታ።


“ነገ በዚህ ጊዜ ከብንያም ምድር አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንዲሆን ቀባው፤ እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋል። እነሆ፤ ሕዝቤን ከላይ ተመልክቻለሁ፤ የስቃይ ጩኸቱ ከእኔ ዘንድ ደርሷልና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች