Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 20:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ንጉሡም በማዘንና በመበሳጨት በሰማርያ ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ተመልሶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 የእስራኤልም ንጉሥ ተበሳጭቶና ተቈጥቶ ሰማርያ ወዳለው ቤተ መንግሥቱ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ንጉሡም በማዘንና በመበሳጨት በሰማርያ ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ተመልሶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 20:43
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፥ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ንጉሦች ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፥ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም።


የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እንዳልህ ነው፥ እኔ ለእኔም የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” አለ።


አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።


አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በጌታ ላይ ይቈጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች