1 ነገሥት 20:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ከዚህም በኋላ እነርሱ በወገባቸው ማቅ ታጥቀው፥ በራሳቸውም ገመድ ጠምጥመው ወደ ንጉሥ አክዓብ በመሄድ “አገልጋይህ ቤንሀዳድ ምሕረት አድርገህ ሕይወቱን እንድታተርፍለት ይማጠንሃል” አሉት። አክዓብም “እርሱ እስከ አሁን በሕይወት አለ ማለት ነውን? ከሆነስ መልካም ነው፤ እንግዲህ እርሱ ለእኔ እንደ ወንድም ነው!” ሲል መለሰላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 እነርሱም በወገባቸው ላይ ማቅ ታጥቀው፣ በራሳቸው ላይ ገመድ ጠምጥመው ወደ እስራኤል ንጉሥ በመሄድ፣ “አገልጋይህ ቤን ሃዳድ፣ ‘እባክህ በሕይወት እንድኖር ፍቀድልኝ’ ብሎ ይለምንሃል” አሉት። ንጉሡም፣ “እስካሁን በሕይወት አለን? ወንድሜ እኮ ነው” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ከዚህም በኋላ እነርሱ በወገባቸው ማቅ ታጥቀው፥ በራሳቸውም ገመድ ጠምጥመው ወደ ንጉሥ አክዓብ በመሄድ “አገልጋይህ ቤንሀዳድ ምሕረት አድርገህ ሕይወቱን እንድታተርፍለት ይማጠንሃል” አሉት። አክዓብም “እርሱ እስከ አሁን በሕይወት አለ ማለት ነውን? ከሆነስ መልካም ነው፤ እንግዲህ እርሱ ለእኔ እንደ ወንድም ነው!” ሲል መለሰላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |